የበርሃ አንበጣ መንጋ የመከላከል ስራውን የሚያግዙ የእስራኤል ባለሙያዎች አዲስ አበባ ገቡ

ከእስራኤል የመጣው የአንበጣ መከላከል ልዩ ግብረ ኃይል

  •   የበርሃ አንበጣ መንጋ የመከላከል ስራውን የሚያግዙ የእስራኤል ባለሙያዎች አዲስ አበባ ገቡ
  •  
     
    ባለሙያዎቹ በኢትዮጵያ የበርሃ አንበጣ መንጋ ስርጭትን የመቆጣጠር ስራ ተሳትፎ የሚያደርጉ ናቸው ተብሏል።
    የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሚስተር ጋቢ አሽኬናዚ የኢትዮጵያ ጠ / ሚ ዶ / ር አብይ አህመድን ጥያቄ ተከትሎ ከኢትዮጵያ አቻዎቻቸው ጋር ተባብረው የበርሃ አንበጣ መንጋን የመከላከል ስራውን የሚያግዙ የእስራኤል ባለሙያዎችን ወደ ኢትዮጵያ ልከዋል።
    የእስራሉ ግብረ ኃይል ከ 2 ቶን በላይ ዘመናዊ መሣሪያዎችን ይዞ የመጣ ሲሆን ፣ ይህም ክዋኔው ሲጠናቀቅ ሁሉንም መሣሪያዎች ለኢትዮጵያ ባለሙያዎች ያስተላልፋል፡፡
    በኢትዮጵያ ቆይታቸዉ ከ200 በላይ ለሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች የበርሃ አንበጣ መከላከል መንገዶች ዙሪያ ስልጣና ይሰጣሉ። በዚህም መሰረት በጂጂጋ ለባለሙያዎች ስልጠና በመስጠት ላይ ይገኛሉ።
     
    ግብረ ኃይሉ በኢትዮጵያ እና በእስራኤል መካከል ያለዉን ለዘመናት የዘለቀ ጠንካራ ግኝኙነት ተምሳሌት ነው።