በ ኮቪድ-19 ወረር ሽኝ ወቅት ወደ እስራኤል ለመጓዝ የተሰጠ መመሪያ

በ ኮቪድ-19 ወረር ሽኝ ወቅት ወደ እስራኤል ለመጓዝ የተሰጠ መመሪያ

  •   እስራኤል ለመግባት የሚፈልጉ የውጭ ዜጎች በኦንላይን በ ኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት የውጭ ዜጎች  ወደ እስራኤል የመግቢያ ፈቃድ ማመልከቻ ቅጽ መሙላት አለባቸው ፡፡
  •  
     
    ኮቪድ-19 ወረር ሽኝ ወቅት ወደ እስራኤል ለመጓዝ የተሰጠ መመሪያ
     
    እስራኤል ለመግባት የሚፈልጉ የውጭ ዜጎች በኦንላይን ኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት የውጭ ዜጎች  ወደ እስራኤል የመግቢያ ፈቃድ ማመልከቻ ቅጽ መሙላት አለባቸው ፡፡
    ቅጹ የግል ማመልከቻ ብቻ ነው ፡፡ በማመልከቻው ላይ አብረዉ ያሉ ተጔዦች ሊታከሉ አይችሉም ለእያንዳንዱ ጓዥ የተለያየ ማመልከቻ መቅረብ አለበት።
    ልብ ይበሉ በማመልከቻው ቅጽ ውስጥ ከዚህ ማመልከቻ ጋር የተዛመዱ ማመከቻ ቁጥሮች ማከ ይችላሉ፡፡
    ቅጹን በሚሞሉበት ጊዜ የሚከተሉትን ጨምሮ ማጣቀሻዎችን እና ደጋፊ ሰነዶችን ማያያዞ ያረጋግጡ:-
    1.     በግልጽ የሚነበብ የአመልካቹ የፓስፖርት ፎቶ ኮፒ
    2.    እንደየሁኔታው የኮቪድ-19 ክትባት መከተብዎን የሚገልጽ የምስክር ወረቀት ወይም  ከኮቪድ-19 ማገገሞን የሚገልጽ የሃኪም ማረጋገጫ
    3.    በማመልከቻው ውስጥ እንደተጠቀሰው ወደ እስራኤል ለመግባት የተጠየቀበት ምክንያት ጋር ተያያዥነት ያላቸው ተጨማሪ ሰነዶች።
    ኦንላይን የማመልከቻ ቅጹን በሚሞሉበት ጊዜ አመልካቹ ያመለክት ወቅት የሚገኝበት አገር መመረጥ አለበት በዚህ መሠረት ማመልከቻው ለምርመራ እና ለሂደቱ የሚላክበት የእስራኤል ኤምባሲ ወይም ቆንስላ የሚገኝበት ቦታ መመረጥ አለበት ፡፡
    አፅንዖት የምንገልጸው ነገር ቢኖር መጨረሻ ካመለከቱበት ቀን ቀጥሎ ባሉት 15 ቀናት ዉስጥ ማመልከት አይቻልም።
    ወደ እስራኤል ለመጓዝ ጥያቄ ለማቅረብ ከዚህ በታች ያለውን አገናኝ ይከተሉ
    https://govforms.gov.il/mw/forms/knisalisrael@mofa.gov.il
    በ ኮቪድ-19 ወረር ሽኝ ወቅት ወደ እስራኤል ለመጓዝ የተሰጠውን መመሪያ በሚከተለው አገናኝ ያገኙታል ፡፡