እስራኤል ታዛቢ ሀገር በመሆን የአፍሪካ ህብረትን በድጋሚ ተቀላቀለች

እስራኤል ታዛቢ ሀገር በመሆን የአፍሪካ ህብረትን በድጋሚ ተቀላቀለች

  •  
     
    የእስራኤል ታዛቢነት በመደበኛ ደረጃ  አፍሪካ ህብረት ጋር መመስረቱ ሁለቱ አካላት በጋራ ኮቪድ-19 ለመዋጋት ፅንፈኛ ሽብርተኝነት በመላው አህጉሪቱ እንዳይስፋፋ ለመከላከል እና ሌሎች ጉዳዮች ላይ መተባበር የሚችሉባቸዉን ምቹ ሁኔታዎች ይፈጥራል።
     
    በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አለልኝ አድማሱ ..  2002 ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ለአፍሪካ ህብረት በታዛቢነት የሹመት ደብዳቤያቸውን ያቀረቡ የመጀመ አምባሳደር ሆነዋል ፡፡
    54 አባል ሃገራት ያሉት የአፍሪካ ህብረት በአፍሪካ አህጉር ዉስጥ ትልቁ እና ተጽኖፈጣሪ ተቋም ነው።
    የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ያኢር ላፒድይህ ለእስራኤል እና ለአፍሪካ ግንኙነቶች ትልቅ የደስታ ቀን ነው... በአፍሪካ አህጉር እና ከድርጅቱ አባል አገራት ጋር የምናደርገውን እንቅስቃሴ ለማጠናከር ይረዳናልብለዋል ፡፡ እስራኤል 46 የአፍሪካ አገራት ጋር ግንኙነት ያላት ሲሆን በንግድ፣ ዕርዳታ እና በየተለያዩ መስኮች እና ትብብር ትሰራለች፡፡
    ከቅርብ ዓመታት ወዲህ እስራኤል ከቻድ እና ከጊኒ ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቷን ያደሰች ሲሆን ሱዳን በበ የአብርሃምን ስምምነት መቀላቀሏን ተከትሎ ከእስራኤል ጋር ግንኙነቷን በመደበኛ ደረጃ መጀመሯን አስታውቃለች ፡፡