ምክትል ከንቲባ ወሮ አዳነች አቤቤ በኢትዮጵያ ከእስራኤል አምባሳደር ጋር ተወያዩ

አምባሳደር ሞራቭ ከምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ጋር ተወያዩ

  •   ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በኢትዮጵያ ከእስራኤል አምባሳደር ጋር ተወያዩ
  •  
     
    የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በኢትዮጵያ ከእስራኤል አምባሳደር ራፋኤል ሞሮቭ ጋር ተወያዩ።
    በውይይታቸውም በትምህርት፣ ዲፕሎማሲ፣ ኢንቨስትመንት፣ በባህልና ቱሪዝም ዘርፎችን በተመለከተ መክረዋል፡፡
    እንዲሁም ከእስራኤል ከተሞች ጋር እህትማማችነት መፍጠርን ጨምሮ ተባብረው ለመስራት በሚያስችላቸው ሁኔታዎች ላይ መነጋገራቸው ነው የተገለጸው፡፡
    ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በኢትዮጵያ ብሎም በመዲናዋ ለሚገኙ ቤተ እስራኤላውያን ያላቸውን አክብሮት በዚሁ ወቅት ገልጸዋል፡፡
    በቀጣይም በከተማዋ እና በእስራኤል መንግስትና ህዝብ መካከል ያለውን ጠንካራ ግንኙነት እና ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር እና ተቀራርበው ለመስራት ዝግጁ ነን ብለዋል።
    አምባሳደር ሞሮቭ በበኩላቸው የኢትዮጵያና እስራኤልን ለዘመናት የቆየ ግንኙነት እና ትብብር አድንቀዋል፡፡
    በቀጣይም በተወያዩባቸው ዘርፎች በጋራ ለመስራት ያላቸውን ፅኑ ፍላጎት መግለጻቸውን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬተርያት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
     
    ምንጭ: ኤፍ ቢ ሲ