እስራኤል ታዛቢ ሀገር በመሆን የአፍሪካ ህብረትን በድጋሚ ተቀላቀለች
-
-
7/23/2021
-
-
GovXContentSection
የእስራኤል ታዛቢነት በመደበኛ ደረጃ ከአፍሪካ ህብረት ጋር መመስረቱ፤ ሁለቱ አካላት በጋራ ኮቪድ-19 ን ለመዋጋት ፣ ፅንፈኛ ሽብርተኝነት በመላው አህጉሪቱ እንዳይስፋፋ ለመከላከል እና ሌሎች ጉዳዮች ላይ መተባበር የሚችሉባቸዉን ምቹ ሁኔታዎችን ይፈጥራል።
በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አለልኝ አድማሱ እ.ኤ.አ ከ2002 ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ለአፍሪካ ህብረት በታዛቢነት የሹመት ደብዳቤያቸውን ያቀረቡ የመጀመሪያዉ አምባሳደር ሆነዋል ፡፡
54 አባል ሃገራት ያሉት የአፍሪካ ህብረት፤ በአፍሪካ አህጉር ዉስጥ ትልቁ እና ተጽኖፈጣሪ ተቋም ነው።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ያኢር ላፒድ “ይህ ለእስራኤል እና ለአፍሪካ ግንኙነቶች ትልቅ የደስታ ቀን ነው... በአፍሪካ አህጉር እና ከድርጅቱ አባል አገራት ጋር የምናደርገውን እንቅስቃሴ ለማጠናከር ይረዳናል” ብለዋል ፡፡ እስራኤል ከ 46 የአፍሪካ አገራት ጋር ግንኙነት ያላት ሲሆን በንግድ፣ ዕርዳታ እና በየተለያዩ መስኮች በአጋርነት እና በትብብር ትሰራለች፡፡
ከቅርብ ዓመታት ወዲህ እስራኤል ከቻድ እና ከጊኒ ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቷን ያደሰች ሲሆን ሱዳን በበኩሏ የአብርሃምን ስምምነት መቀላቀሏን ተከትሎ ከእስራኤል ጋር ግንኙነቷን በመደበኛ ደረጃ መጀመሯን አስታውቃለች ፡፡
-
-
-
-
-
-
-
-
-
-
-
-
-
-
-
-
-
-
-