ወ/ሮ ፈንታይ አለሙ በኢትዮጵያ የእስራኤል ምክትል አምባሳደር ናቸው። ወ/ሮ ፈንታይ አዲስ አበባ በሚገኘው የእስራኤል ኤምባሲ ውስጥ መሰረት አድርገዉ በተለያዩ መስኮች እስራኤል ከኢትዮጵያ ጋር ስላላት የሁለትዮሽ ግንኙነት፣ በቀጠናዉ ስላሉ የተለያዩ ጉዳዮች እና ስትራቴጂካዊ ጉዳዮችን ሸፍነው ይሰራሉ። ወ/ሮ ፈንታይ ወደ አዲስ አበባ ከመምጣታቸው በፊት በቺሊ በሚገኘው የእስራኤል ኤምባሲ ምክትል አምባሳደር ሆነው ያገለገሉ ሲሆን ከዚያ በፊት በእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዋና መሥሪያ ቤት አገልግለዋል።
ወ/ሮ ፈንታይ ከዲፕሎማሲያዊ ሥራቸው በፊት በራፋኤል አድቫንስድ ሚሊተሪ ዲፌንስ ሲስተም ሊሚትድ እ.ኤ.አ ከ2010–2017 የድርጅቱ ተቋማዊ እድገት ዳይሬክተር የነበሩ ሲሆን እ.ኤ.አ ከ 2002 እስከ 2010 ባለው ጊዜ ውስጥ በሦስት የተለያዩ የእስራኤል ኩባንያዎች የአስተዳደር ቦታን ይዘው ሰርተዋል። ወ/ሮ ፈንታይ ገሊላ ከሚገኘው ኤመክ ይዝሬኤል ኮሌጅ የመጀመሪያ ዲግሪያቸዉ በመአረግ ያገኙ ሲሆን ከተመሳሳይ ተቋም በልማት እና ድርጅት አማካሪነት የማስተርስ ዲግሪያቸዉን ይዘዋል።