ማሻቭ

ማሻቭ

  •  
     
    የእስራኤል ይፋዊ ዓለም አቀፍ የልማት ትብብር መርሃ ግብር የተጀመረው 1957 መጨረሻ ላይ ሲሆን። ከተቀረው ታዳጊ ዓለም ጋር ለእስራኤል ፈጣን ልማት መሠረት የሆነውን ዕውቀትና ቴክኖሎጂን ለማካፈል ዓላማን ይዞ ነው ፡፡ ማሻቭ የእስራኤል የልማት ትብብር ኤጀንሲ የዕብራይስጥ ምህፃረ ቃል ሆን የተቋቋመውም እንደ አንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ክፍል ነበር፡፡
    መርሃግብሩ ሲጀመር እስራኤል ራሷ ገና በማደግ ላይ ያለች ሀገር በነበረችበት ወቅት ሲሆን በሰው አቅም ግንባታ ላይም አተኩሮ መሰረታዊ የሰዉ ሃይል አቅም ግንባታ ላይ ያተኮረ ነበር ፡፡ ጅማሮው ትንሽ ቢመስልም አሁን ላይ ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ እና አካባቢያዊ ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥን በመላው የታዳጊው ዓለም ወደ ሰፊ የትብብር ፕሮግራም አድጓል ፡፡
    ማሻቭ ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ በግምት በእስራኤል እና በውጭ  132 ሀገሮች ወደ 270,000 የሚጠጉ የኮርስ ተሳታፊዎችን ያሰለጠነ ሲሆን በዓለም ዙሪያ ደግሞ በርካታ የማሳያ ፕሮጀክቶችን አዘጋጅቷል።
     
    ያግኙን:- 
    MASHAV@addisababa.mfa.gov.il 
     
  •