ምክትል አምባሳደር

ምክትል አምባሳደር

  •  
     
    / ፈንታይ በኢትዮጵያ የእስራኤል ምክትል አምባሳደር ናቸው። ወ/ሮ ፈንታይ አዲስ አበባ በሚገኘው የእስራኤል ኤምባሲ ውስጥ መሰረት አድርገዉ በተለያዩ መስኮች እስራኤል ከኢትዮጵያ ጋር ስላላት የሁለትዮሽ ግንኙነት፣ በቀጠናዉ ስላሉ የተለያዩ ጉዳዮች እና ስትራቴጂካዊ ጉዳዮችን ሸፍነው ይሰራሉ። ወ/ ፈንታይ ወደ አዲስ አበባ ከመምጣታቸው በፊት በቺሊ በሚገኘው የእስራኤል ኤምባሲ ምክትል አምባሳደር ሆነው ያገለገሉ ሲሆን ከዚያ በፊት በእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዋና መሥሪያ ቤት አገልግለዋል።
    ወ/ሮ ፈንታይ ከዲፕሎማሲያዊ ሥራቸው በፊት በራፋኤል አድቫንስድ ሚሊተሪ ዲፌንስ ሲስተም ሊሚትድ .ኤ. 2010–2017 የድርጅቱ ተቋማዊ እድገት ዳይሬክተር የነበሩ ሲሆን እ.ኤ.አ ከ 2002 እስከ 2010 ባለው ጊዜ ውስጥ በሦስት የተለያዩ የእስራኤል ኩባንያዎች የአስተዳደር ቦታን ይዘው  ሰርተዋል። ወ/ሮ ፈንታይ ገሊላ ከሚገኘው ኤመክ ይዝሬኤል ኮሌጅ የመጀመ ዲግሪያቸዉ በመአረግ ያገኙ ሲሆን ከተመሳሳይ ተቋም በልማት እና ድርጅት አማካሪነት የማርስ ዲግሪያቸዉን ይዘዋል።