ውድ እንግዳችን ከታች የተዘረዘሩትን ሁሉንም መስፈርቶችን ሟሟላቶን ያረጋግጡ:: ቧልተሟሉ ዶክመንቶች አገልግሎታችንን ማግኘት አንደማይችሉ በአክብሮት እንገልጻለን::
አጠቃላይ ሁኔታዎች:
1. በአዲስ አበባ የሚገኘው የእስራኤል ኤምባሲ ለሁሉም ሃገር ለዜጐች ቪዛ ይሰጣል
2. ሁለት በቅርቡ የተነሳ ፣ ግልጽ ፣ ነጭ የጀርባ ላይ የተነሳ የፓስፖርት ሳይዝ ፎቶ
3. ለሁሉም የቪዛ ዓይነቶች, የቪዛ ማመልከቻ ፎርም መሙላት አለብዎት:: በተጨማሪም ሁሉንም አስፈላጊ ሰነዶች (የኦርጅናል ኮፒዉን ጨምሮ) ማስገባት ይኖርቦታል:: እያንዳንዱ ግለሰብ የራሱን / የራሷን ቅጽ መሙላት እና መፈረም ይኖርባቸዋል::
4. ለቪዛ የሚያመለክት ማንኛውም ግለሰብ ወደ ኤምባሲው በመምጣት የግል ቃለ መጠይ ማድረግ ይጠበቅበታል::
የቤተሰቡን ወጪዎች ለመሸፈን የሚያስፈልጉ መሰረታዊ ሁኔታዎች:
1. ሁለት በነጭ የጀርባ ላይ ብቻ የተነሳ 5 በ 4 ሳ.ሜ የተነሳ የፓስፖርት ፎቶ
2. የውጭ አገር ፓስፖርት ኮፒ እና ቋሚ የነዋሪነት መታወቂያ
3. ከአሠሪዎ የሥራ መደብደ እና ደመወዝን የሚገልፅ ደብዳቤ
4. በግል ስራ ላይ የተሠማሩ ከሆነ የንግድ ፈቃድ ኮፒ( አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ወደ እንግሊዝኛ ይተረጎማል)
5. የ6 ወር የባንክ ስቴትመንት
6. የቤተሰቡን ስም እና ፓስፖርት ቁጥር የመግለጽ የድጋፍ ደብዳቤ
7. የሆቴል ቦታ የተያዘበት ማረጋገጫ(ቢያንስ የግማሽግዜ ቆይታ ክፍያ መከፈል ይኖርበታል)
8. የበረራ ቲኬት ማረጋገጫ)ቡኪግ ተቀባይነት ኣለው)
9. ለሚቆዩበት ጊዜ የጉዞ ዋስትና
የቪዛ መስፈርቶች
ቪዛ በሚያመለክቱበት ጊዜ የሚከተሉትን ሰነዶች የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተረጋገጡ መሆን አለባቸው
· ለልጆች የልደት ምስክር ወረቀት
· ካገቡ የጋብቻ የምሥክር ወረቀት ወይም ካላገቡ ደግሞ ያላገባየምሥክር ወረቀት
· የንግድ ፈቃድ
· የመኪና የባለቤትነት
· ሁሉንም የተተረጎሙ ሰነዶች
ሀ2 - የተማሪ ቪዛ መስፈርቶች
1. መርሃግብሩ ከተጠናቀቀ በኋላለስድስት ወር የሚያገለግል ፓስፖርት
2. ሁለት በነጭ የጀርባ ላይ ብቻ የተነሳ 5 በ 4 ሳ.ሜ የተነሳ የፓስፖርት ፎቶ
3. ለቆይታው የመጀመሪያ ወር የሚያገለግል የጉዞ ኢንሹራንስ
4. የምዝገባ ፎርም ከድረ-ገጻችን ላይ ማውረድ እና መሙላት- ሀ2 - የተማሪ ቪዛ ፎርሙላይ መግለጽ
5. በእስራኤል ከሚገኝ ዩኒቨርሲቲ የሚከተሉትን ያሟላ የቅድሚያ የግብዣ ደብዳቤ
- ክፍሉ
- ቦርድ
- የጤና ኢንሹራንስ እና
- የመጀመሪያና ማጠናቀቅያ ቀን
6. ለኢትዮጵያውያን ዜጎች የቪዛ ክፍያ 566 ብር ሲሆን ክፍያው በቆንላው የሂሳብቁጥር ገቢተደርጎ ደረሰኙ
ከላይ ከተዘረዘሩት ሰነዶች ጋር አያይዞ ማቅረብ
7. ኢትዮጵያውያን ላልሆኑ ዜጎች የ የቪዛ ክፍያ 25 ዶላር ሲሆን ክፍያው በቆንላውየዶላር የሂሳ ብቁጥር ገቢ
ተደርጎ ደረሰኙ ከላይ ከተዘረዘሩት ሰነዶች ጋር አያይዞ ማቅረብ
እባክዎን ዶክመንቱን በ ዲኤችኤል(DHL)በኩል የሚልኩ ከሆነ ለመመለስ ክፍያውንም ጨምረው ይክፈሉ
የቪዛውን ማህተም ከተመታ በኋላ ፓስፖርትዎን ወደ እርስዎ እንልክልዎታለን.
ለ / 2- ጎብኚዎች ቪዛ መስፈርቶች
1. ሁለት በነጭ የጀርባ ላይ ብቻ የተነሳ 5 በ 4 ሳ.ሜ የተነሳ የፓስፖርት ፎቶ
2. የጉዞ ፕሮግራም (ሆቴል ቦታ ማስያዝ፣ የደርሶመልስ ትኬት፣ በእስራኤል ውስጥ የጉብኝት ቦታዎች ዝርዝር፣ እና የ ቆይታ ጊዜ)
3. ከአሠሪዎ የሥራ መደብደ፣የእረፍት ግዜ እና ደመወዝን የሚገልፅ ደብዳቤ
4. የተረጋገጠ የመስሪያ ቤቶዏ የሥራ ፍቃድ
5. በባንኩ ሥራ አስኪያጅ ተፈርሞ ማህተም የተደረገበት የባንክ ደብተር እና የባንክ ስቴትመንት
6. ተጋብዘው ከሆነ የሚሄዱት የግብዣ ደብዳቤ
7. ባለትዳር እና ልጆች ካልዎት የጋብቻ እና የትውልድ ሰርቲፊኬት ኦሪጅናል ማቅረብ
8. ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኝ የኢንሹራንስ ኩባንያ የጉዞ ዋስትና
9. በግል ስራ ላይ የተሰማሩ ከሆነ እና አንደ መኪና እና ቤት ያሉ ንብረቶች ካለዎት የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት እና የባለቤትነት ሰነዶች:: ለንግድ ስራዎ የሚጠቀሙበት የባንክ ቁጥር እና ሌሎች ተዛማጅ ሰነዶች::
10. የፖሊስ የነጻ የምስክር ወረቀት
ወደ እስራኤል የንግድ ጉዞ ለ መስፈርቶች:
1. ሁለት በነጭ የጀርባ ላይ ብቻ የተነሳ 5 በ 4 ሳ.ሜ የተነሳ የፓስፖርት ፎቶ
2. የጉዞ ፕሮግራም (ሆቴል ቦታ ማስያዝ፣ የደርሶመልስ ትኬት፣ በእስራኤል ውስጥ የጉብኝት ቦታዎች ዝርዝር፣ እና የ ቆይታ ጊዜ)
3. ባለትዳር ከሆኑና እና ልጆች ካልዎት የጋብቻ እና የልደት የምስክር ወረቀት ኦርጂናል ኮፒ ማቅረብ
4. የባንክ ሥራ አስኪያጅ ማህተም እና ፊርማ ያለበት የኩባንያዎ የባንክ ሂሳብ ቁጥር
5. በእስራኤል ውስጥ ያለ የንግድ ኣጋር ጋር የነበረ ግንኙነት እውቂያዎች የደብዳቤ
6. በመደበኛ የንግድ እንቅስቃሴን የሚያሳይ ሰነዶች
7. ከኩባንያዎ የተጻፈ የጉብኝትዎ አላማ የሚገልጽ ደብዳቤ
8. ተጋብዘው ከሆነ የሚሄዱት የግብዣ ደብዳቤ
9. በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኝ የኢንሹራንስ ኩባንያ የጉዞ ዋስትና
ህክምና ቪዛ ሐ መስፈርቶች:
1. ለ 6 ወራት ላላነሰ ጊዜ የሚሰራ ህጋዊ ፓስፖርት
2. ሁለት በነጭ የጀርባ ላይ ብቻ የተነሳ 5 በ 4 ሳ.ሜ የተነሳ የፓስፖርት ፎቶ
3. ከሆስፒታል መደበኛ ደብዳቤ
4. የሆቴል ቦታ ማስያዧ
5. የበረራ ቲኬት
6. የጉዞ ኢንሹራንስ
7. ለህክምና ክፍያ ክፍያ ማረጋገጫ
የእስራኤል ጉብኝት ግብዣ:
በዘመድ / ድርጅቶች / ኩባንያዎች የተጋበዙ ሰዎች በእስራኤል ውስጥ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል መጋበዝ ኣለባቸው::
ግብዣው ከተረጋገጠ እና ወደ ኤምባሲ ከመጣ በሁኣላ ፣ ተጋባዡ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ወደ ኤምባሲ ይዞ መምጣት ኣለበት::
1. ሁለት በነጭ የጀርባ ላይ ብቻ የተነሳ 5 በ 4 ሳ.ሜ የተነሳ የፓስፖርት ፎቶ
2. ቪዛ ኣመልካቹ ለተፈቀደለት የግዜ ገደብ የደርሶ መልስ የበረራ ትኬት
3. የጉዞ ዋስትና
4. የግብዣ ደብዳቤ እና የሞባይል ቁጥር
5. የጠሪው የእስራኤል መታወቂያ ኮፒ
የቪዛ ክፍያ ተመላሽ የማይሆን 680.00 ብር ነው:: የክፍያው ደረሰኝ ከማመልከቻው ጋር ተያይዞ መግባት ኣለበት::
ክፍያው በህብረትባንክ ብቻ መከናወን አለበት::
ማሳሰቢያ፡- ተጨማሪ ማስረጃዎች ሊጠየቁ ይችላሉ፡፡ እባኮ ቪዛ ከመጠየቆ በፊት የታሙኣላ ማስረጃ እንዳሎት ያረጋግጡ :: በተጨማሪም ሁሉም ከላይ የተጠከሱ ሰነዶች ካልተሞሉ ማመልከቻዎ ተቀባይነት ኣይኖረዉም::