አጠቃላይ መረጃዎች

አጠቃላይ መረጃዎች

  •    
    በአዲስ አበባ የሚገኘው የእስራአል ኤምባሲ የቆንስላ ጽ / ቤት ለሁሉም አገር  ዜጎች ቪዛ ይሰጣል
  •  
     
     አጠቃላይ ሁኔታዎች:
     
    1.በአዲስ አበባ የሚገኘው የእስራኤል ኤምባሲ ለሁሉም ሃገር ለዜጐች ቪዛ ይሰጣል
     
    2.  ፓስፖርትዎ ወደ እስራአል ከመግቢያዎ ቀን አንስቶ ቢያንስ ለ ፮(6) ወራት ተቀባይነት ያለው መሆን አለበት
     
    3.  ለሁሉም የቪዛ ዓይነቶች, የቪዛ ማመልከቻ ፎርም መሙላት አለብዎት በተጨማሪም ሁሉንም አስፈላጊ ሰነዶች (የኦርጅናል ፎቶግራፍ ቅጂን ጨምሮ) ማስገባት ይኖርባቸዋል:: እያንዳንዱ ግለሰብ  የራሱን / የራሷን ቅጽ መሙላት እና መፈረም ይኖርባቸዋል::
     
    4.  ለቪዛ የሚያመለክት ማንኛውም ግለሰብ ወደ ኤምባሲው በመምጣት የግል ቃለ መጠይ ማድረግ ይጠበቅበታል
     
     
    የቤተሰቡን ወጪዎች ለመሸፈን የሚያስፈልጉ መሰረታዊ ሁኔታዎች:
    1.       የውጭ አገር ፓስፖርት ኮፒ እና ቋሚ የነዋሪ መታወቂያ
    2.       ከአሠሪዎ የሥራ መደብደ እና  ደመወዝ የሚገልፅ  ደብዳቤ
    3.       በግል ስራ ላይ የተሠማሩ ከሆነ የንግድ ፈቃድ ኮፒ, አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ወደ እንግሊዝኛ ይተረጎማል
    4.       6 ወር የባንክ ስቴትመንት
    5.       የቤተሰቡን የቤተሰብ ስም እና ፓስፖርት ቁጥር የመግለጽ የድጋፍ ደብዳቤ
    6.       የሆቴል ቦታ የተያዘበት  ማረጋገጫ
    7.       የበረራ ቲኬት ማረጋገጫ.
    8.       ለሚቆዩበት ጊዜየ ጉዞ ዋስትና 
     
    ቀጠሮ ለማስያዝ, የሚከተለውን ድህረ-ገፅ ይጎብኙ  

     

     
     
    የቆንስላ ጽ / ቤት ለሚጎበኙ ሰዎች የደህንነት መመሪያዎች
    1.  እባክዎ የፎቶ መታወቂያ ይዘው ይቅረቡ
    2.  እያንዳንዱ ጎብኚ እና ንብረቶች የደህንነት ፍተሻ ይደረግባቸዋል
    3.  ለ ደህንነት ሲባል ማንኛዉም የግል ንብረት የእጅ ቦርሳዎች, ሞባይል ስልኮች እና የኤሌክትሮኒክ መሣሪያዎች ውደ ኤምባሲው ጊቢ ዉስጥ ኣይገቡም 
    4.  ትልቅም ሆነ ትናንሽ ቦርሳዎችን ወይም ሻንጣዎችን ይዘው ወደ ኤምባሲው ኣይምጡ
     
    5.  ምግብ ወይም መጠጥ ጠርሙሶች ወይም ዕቃዎችን ይዘው ወደ ኤምባሲው ኣይምጡ
     6.  በ ኤምባሲው የደህንነት መመሪያዎች በ ኮንስላ መጠበቂያ ክፍል ዉስጥም ተግባራዊ ስለሚሆኑ፣ማናቸዉም ከ ደህንነት የሚመጡ ዛዞች መከበር አለባቸው

     

    በውጭ አገር ለሚኖሩ እስራኤላዊያን ምዝገባ 

     
     እስራኤልዊ ዜጋ ከሆኑ እና ወደ ውጭ አገር ሲጓዙ ከቆዩ ከዚህ በታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ  በማድረግ የምዝገባ ፎርሙን ያቅርቡ ቀጥሎም የሚያገኙትን ፎርም በመሙላት ያስገቡ 

    በውጭ አገር ለሚኖሩ እስራኤላዊያን ምዝገባ ፎርም

     
     

    አድራሻ

    በየካ ክፍለ ከተማ, ቀበሌ 22, የቤት ቁጥር. 283
    ስልክ ቁጥር: +251-11-6-461948 እባክዎን ከ ጠዋቱ ፫ ሰኣት እስከ ፬ ሰኣት  ከሰኞ እስከ ዓርብ ባለው ጊዜ ዉስጥ ብቻ ዪደውሉ::

    ፋክስ ቁጥር:+251-11-6461961 

    ኢሜል:   consular@addisababa.mfa.gov.il

                  consular3@addisababa.mfa.gov.il

     .. ቁጥር 1266, አዲስ አበባ

     

     

    የ ኮንስላ ኣገልግሎት መቀበያ ሰኣቶች

    ከሰኞ - ሐሙስ 4:00AM- 7:00PM

    አርብ - 4:00AM - 5:00PM

    አርብ - 5:00AM - 7:00AM ድኤንኤ ምርመራ

    ኮንስላ  አገልግሎቶች የስልክ የመቀበያ ሰዓቶች

    ከሰኞ - ሐሙስ 3:00AM - 4:30AM 

    ስልክ ቁጥር: +251-11-6-461948

    የሰነድ መመላሽ ሰዓቶች

    ከሰኞ - ሐሙስ 10:00PM

    አርብ 7:00PM