First Ethiopian business delegate visits Israel
-
-
3/19/2013
-
-
GovXContentSection
Israel – The first private business delegation consisting of Ethiopian businessmen and women made an official visit to Israel during March 17-20, 2013.
The venture was made in a bid to bring Israel's technology and smart ideas to businesses in Ethiopia by way of partnering with the Ethiopian businesses and people. As an eye opening experience, the visit has successfully undertaken seminars, business to business meetings, and official business tours in Israel.
(Above) Chronicle by The Ethiopian Herald newspaper
የኢትዮጵያ የመጀመሪያው የንግድ ልዑካን ቡድን በእሥራኤል ጉብኝት አደረገ ::
አዲስ አበባ መጋቢት 16/2005 የኢትዮጵያ የመጀመሪያው የንግድ ልዑካን ቡድን በእሥራኤል ጉብኝት ማድረጉን የአገሪቱ ኤምባሲ ዛሬ አስታወቀ። በኢትዮጵያ የእሥራኤል ኤምባሲ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጸው የኢትዮጵያ ንግድ ማህበረሰብን የሚወክሉ ዘጠኝ ድርጅቶች ባለፈው ሳምንት ጉብኝት አድርገዋል። የአገሪቱን ቴክኖሎጂ የንግድ አሰራሮችን ለመቅሰም የተሰማራው 12 አባላት ያለው ቡድን በቆይታው ከጉብኝቱ በተጨማሪ በሴሚናሮችና በውይይት ላይም ተሳትፏል። በጉብኝቱ ከአግሮ-ኢንዱስትሪ፣ከአውቶሞቲቭ፣ከሆቴልና ቱሪዝም፣ከኃይል ኢንዱስትሪና ሁለገብ የንግድ እንቅስቃሴ የተሰማሩ ድርጅቶች መሳተፋቸውን መግለጫው ያስረዳል። የባዮጄኒክ ቢዩቲ ሳሎንና የጂ ኤም ኤም ጋርመንት ኩባንያዎች ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወይዘሮ ሙሉእመቤት ገብረ ሥላሴ በሰጡት አስተያየት ጉብኝቱ በአገሮቹ የንግድ ድርጅቶች መካከል ያለውን ግንኙነት ለማሳደግ ጥሩ መሠረት ማስቀመጡን ተናግረዋል። የእሥራኤል ኩባንያዎች ለሥራ ያላቸው ተነሳሽነትና አደረጃጀት መልካም ሆኖ እንዳገኙትም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጉብኝቱን በማደራጀትና የልምድ ልውውጥ ወይይት እንዲካሄድ ያደረገው እንቅስቃሴ አስመስጋኝ መሆኑንም ወይዘሮ ሙሉእመቤት አስታውቀዋል። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን የኮርፖሬት ፕላኒንግ ዳይሬክተር አቶ መኩሪያ ቱሉ በበኩላቸው ጉብኝቱ በኢትዮጵያ በኩል ሲካሄድ የመጀመሪያው መሆኑን ገልጸው፣በጉብኝቱ የአገሪቱ ኩባንያዎች ወደዚህ መጥተው ለመስራትና ግንኙነቱን በሚያጠናክሩ መንገዶች ላይ መነጋገራቸን ገልጸዋል። ጉብኝቱ በአገሪቱ የኃይል ልማት የሚሳተፉ ኩባንያዎችን ለማወቅና ተባብሮ ለመስራት የሚያስችል ግንኙነት ለመፍጠር እንደሚረዳም አስረድተዋል። የእሥራኤል ኩባንያዎች በተበጣጠሰ መልኩ በመምጣት ያደርጉት የነበረውን እንቅስቃሴ በተደራጀ መልኩ በማከናወን በዘርፉ በማምረቻና በኃይል ማሰራጫ ዘርፎች ለመሰማራት እንደሚረዳቸውም ተናግረዋል። በሁለቱ አገሮቹ መካከል ያለው የንግድ ልውውጥ በዓመት ከ83ሚሊዮን ዶላር በላይ ደርሷል። አገሮቹ ባለፉት ሰባት ዓመታት ያደረጉት የንግድ ልውውጥ ከግማሽ ቢሊዮን ዶላር መድረሱን ከኤምባሲው የተገኘውን መግለጫ ጠቅሶ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዘገባ ያመለክታል። ኢትዮጵያና እሥራኤል ንግሥት ሳባ የእሥራኤሉን ንጉሥ ሰለሞን ከጎበኘችበት ዘመን ጀምሮ የሚቆጠር ከ3ሺህ ዓመታት በላይ የዘለቀ ግንኙነት አላቸው።
(Above) chronicle by the Ethiopian News Agency
-
-
-
-
-
-
-
-
-
-
-
-
-
-
-
-
-
-
-